የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ - ብሔራዊ መረጃ ማዕከል

Nested Applications

የገቡ ህትመቶች

 

 

የገቡ ህትመቶች

ህትመቶች

Asset Publisher

null የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሀገራዊና ሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ታዜር /እግዚአብሔር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተፈራርመዋል።

የብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ታዜር /እግዚአብሔር በፊርማ ሥነሥርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ከዕለታዊ ስራዎች ጀምሮ በስትራቴጂካዊ ጉዳዬች ዙሪያ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በጋር ይሠራል።

የመግባቢያ ስምምነቱ የትብብር ሥራዎቹ ስርዓት የያዙና በሰነድ የተደገፉ እንዲሆኑ ያግዛል።

ስምምነቱ ኢትዮጵያን ከተለያዩ ሃገራት የምታደርገዉን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚረዱ ተግባራትን ለማጠናከር እንደሚያስችላት አቶ ታዜር አብራርተዋል።

በተጨማሪም ሁለቱ ተቋማት ለፖሊሲ ግብዕት የሚሆኑ ሃሳቦችን በጋራ ለማመንጨት የተመቻቸ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸዉ ገልጸዋል።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በበኩላቸው፤ ሁለቱ ተቋማት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በመፈፀም በኩል በሥራ የሚገናኙባቸው ጉዳዮች በርካታዎች መሆናቸውን አንስተዋል።

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ቢሮም ጭምር በመጋራት በትብብር የሚወጧቸው ተልዕኮዎች መኖራቸውንና በተለያዩ የሥራ እንቅስቃሴዎችም የመረጃ ልውውጥ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።

የእስካሁኖቹ የጋራ ሥራዎች ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በሁለቱ ተቋማት አመራሮች ቁርጠኝነት ላይ ብቻ ተመስርቶ የነበረውን የትብብር ግንኙነት በሰነድ የተደገፈ ለማድረግ የመግባቢያ ስምምነቱ መፈረሙን ገልጸዋል።

ስምምነቱ ዲፕሎማቶች የሀገር ጥቅምና ብሔራዊ ደኀንነት በማስጠበቅ ረገድ በቂ ዝግጅት እንዲኖራቸው ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሚያገኟቸውን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንደሚያጠናክርለት ማብራራታቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን የላከው  መረጃ   ያመለክታል።