“ወዳጅ እንዲኮራ፣ ጠላት እንዲፈራ መስራት ብቻ ሳይሆን የሰራነውን ማሳየት አለብን‘ አቶ ተመስገን ጥሩነህ - ብሔራዊ መረጃ ማዕከል

Nested Applications

የገቡ ህትመቶች

 

 

የገቡ ህትመቶች

ህትመቶች

Asset Publisher

null “ወዳጅ እንዲኮራ፣ ጠላት እንዲፈራ መስራት ብቻ ሳይሆን የሰራነውን ማሳየት አለብን‘ አቶ ተመስገን ጥሩነህ

ወዳጅ እንዲኮራ፣ ጠላት እንዲፈራ፤ ወዳጅ እንዲተማመን፣ ጠላት እንዲመነምን መስራት ብቻ ሳይሆን የሰራነውን ማሳየት አለብን ሲሉ የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡ 

በብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባለቤትነት በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራውንስሮቹየተሰኘና አገርን ለመታደግ የተካሄደ የጀግነት ተጋድሎን የሚያሳየው ፊልም ማክሰኞ ግንቦት 2015 ዓም በንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ህንፃ ተመርቋል። ፊልሙን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ መርቀው አስጀምረውታል።

 የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ በፊልም ምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ ንስሮቹ የተሰኘው ፊልም ኢትዮጵያ የጀግንነት ታሪኳን እየሰነደች መሆኑን የሚያሳይ ስራ ነው።

የኢትዮጵያ ጀግኖችም የሰሩትን የተጋድሎ ስራ ወዳጅም ጠላትም እንዲያውቀው ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ያደጉ አገሮች በመረጃና ደኅንነት ዙሪያ የሚያከናውኑት ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ የጸጥታና  የደኅንነት  ተቋሞቻቸውን ምስልና ገጽታ የገነቡት በኪነ ጥበብ ስራዎችም ጭምር ነው ሲሉ አስረድተዋል።

አቶ ተመስገን እንዳስታወቁት፤ፊልሙ የማድረግ አቅሙ በየጊዜው እየላቀ ያለ ተቋም እየተገነባ እንዳለ በጥበብ ለማሳየት ታልሞ የተሰራ ነው።

በብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አገርን የሚያኮሩ በርካታ አስደናቂ ታሪኮች ተሰርተዋል ያሉት አቶ ተመስገን፤ ንስሮቹ የተሰኘው ፌልም በየዕለቱ ከሚሰሩ አገራዊ ተጋድሎዎች አንዱን ሰበዝ መርጦ ለዕይታ ያበቃ ነው ብለዋል።

ወዳጅ እንዲኮራ፣ ጠላት እንዲፈራ፤ ወዳጅ እንዲተማመን፣ ጠላት እንዲመነምን መስራት ብቻ ሳይሆን የሰራነውን ማሳየት አለብንም ሲሉ ተናግረዋል።

ፊልሙ የጀግንነት ታሪክ ላይ ትኩረት አድርጎ መሰራቱን ጠቁመው፤ የጥበብ ስራው ተዘጋጅቶ ለዕይታ መብቃቱ የጸጥታ ተቋማትን ተቋማዊ ልምድ የቀየረ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ጥንካሬ በዜጎቿና በተቋሞቿ ጥንካሬ እንደሚወሰን ገልፀው፤ በተለይ የጸጥታ ተቋሞቿ በአራት ጉዳዮች ላይ መሰረት መያዝ አለባቸው ብለዋል። እነዚህም መሰረቶች የተቋሞቹ ሰራተኞች፣ ዜጎች፣ወዳጆችና በጠላቶች ልብ ውስጥ መሰረት መያዝ ይገባል ብለዋል።

ንስሮቹ የተሰኘው ፊልም የተቋሙን አጠቃላይ ቁመና በሁሉም ልብ ውስጥ መሰረት የሚያስይዝ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የኢትዮጵያን የጸጥታ ተቋማት አገር የመጠበቅ የጀግንነት ታሪክ ለህዝብ ለማድረስ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የፊልም ኢንዱስትሪ ተዋናዮች የኢትዮጵያን የተቋማት ጥንካሬ በዜጎች ልብ ውስጥ የማስረጽ ሥራ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በፊልም ምረቃ ስነ-ስርዓቱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በምረቃው ስነስርዓቱ ላይ ፊልሙ በተሳካ ሁኔታ እንዲሰራ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅናና ሽልማት ተበርክቷል፡፡ምንጭ :- የኢትዮጵያ ፕሬስ  ድርጅት )