በኢኮኖሚ ደኅንነት እና በጉምሩክ የሕግ ማስከበር የሚደረጉ ስምሪቶች ሙስናንና የኢኮኖሚ አሻጥሮችን ለመከላከል ከፍተኛ ሚና እንደሚያበረክቱ ተገለጸ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሥር የሚገኘው ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በኢኮኖሚ ደኅንነት እና በጉምሩክ ኮሚሽን የሕግ ማስከበር መረጃ ኪነሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች አስመርቋል፡፡

 

ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ የመረጃ ኪነ ሙያ ሰልጣኞችን ባስመረቀበት መርሃግብር የተገኙት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ሲሳይ ቶላ እንደገለጹት፤ ሀገሪቱ በያዘችው 10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ መሰረት መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ በምታደርገው ጥረት በኢኮኖሚ ዘርፍ ያለው የመረጃ ስምሪት ከፍትኛ ድርሻ አለው።

 

ለኢኮኖሚ ደኅንነት ጀማሪ የመረጃ ኦፊሰሮችና ለጉምሩክ ኮሚሽን የሕግ ማስከበር መረጃ ኦፊሰሮች የተሰጠው ስልጠና በሀገራችን በተለይም በኢኮኖሚው መስክ መልካቸውን እየቀያየሩና እየተወሳሰቡ የመጡትን የሙስና፣ የኢኮኖሚ አሻጥርና ተያያዥ ወንጀሎችን ለመለየት፣ ለመከታተልና ለማምከን ከፍተኛ ሚና እንደሚያበረክቱ ገልጸዋል፡፡

 

መንግሥት በአሁኑ ወቅት በኢኮኖሚ ዘርፍ የሚፈጸሙ አሻጥሮችና የሙስናን ድርጊቶችን ለመከላከል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ያመለከቱት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራሉ፤ በዚህ ወቅት ለመመረቅ የበቁት ሰልጣኞች በሚሰማሩበት መስክ ሀገርንና ሕዝብን በማስቀደም በጥብቅ ሙያዊ ስነምግባር የሚሰጠቸውን ስምሪት በብቃት መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

 

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጉሙሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሙሉጌታ በየነ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ያለበትን ብቁ የሰለጠነ የሰው ኃይል ችግር ለመቅረፍ ከብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ጋር በጥምረት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የሕግ ማስከበር መረጃ ዘርፍ የሰለጠኑት ባለሙያዎች በዘርፉ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ትልቅ አገዛ እንደሚያበረክቱ ጠቁመው፤ ኮሚሽኑ ሀገሪቱን እየተፈታተነ ያለውን የኢኮኖሚ አሻጠር ለመግታት በሚደርገው ጥረት ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር የጀመረውን የቅንጅት ሥራ አጠናክሮ ይቀጠላል ብለዋል።

 

ተመራቂዎች በበኩላቸው በቀሰሙት የንድፈ ሀሳብና የተግባር ልምምድ የሀገርና ሕዝባቸውን ደኅንነት ለመጠበቅ በሚሰጣቸው ስምሪት ተልዕኳቸውን በብቃት ለመወጣት ዝግጁ እንደሆኑ መናገራቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢፕድ በላከው መረጃ አመልክቷል።

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች