የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከጀርመን የመረጃና ደኀንነት ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት ስምምነት አደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከጀርመን የመረጃና ደኀንነት ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን ውይይት ማድረጉና መስማማቱን ገለጸ።

በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የልዑካን ቡድን ከጀርመን የመረጃና ደኀንነት ተቋማት የልዑካን ቡድን ጋር በነበረው ቆይታ በቀጣናዊ፣ ዓለም አቀፋዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝርና በጥልቀት ተወያይቷል።

ከውይይቱ በኋላም ተቋማቱ በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያና የጀርመን የመረጃና የደኅንነት ተቋማት ሽብርተኝነትን፣ ሕገ-ወጥ የገንዘብና የሰዎች ዝውውርን እንዲሁም ሌሎችንም ወንጀሎች በጋራ ለመከላከል የመረጃ ልውውጥ ማድረግም የስምምነታቸዉ አካል መሆኑን የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት አገልገሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከዉ መረጃ አመልክቷል።

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች