የኢትዮጵያና ኬንያ የመረጃና ደኅንነት ተቋማት ሽብርተኝነት፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና የተደራጁ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ተስማሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያና ኬንያ የመረጃና ደኅንነት ተቋማት ሽብርተኝነት፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና የተደራጁ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል መስማማታቸውን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።

 

ከጊዜ ወደ ጊዜ በምስራቅ አፍሪካ እየተስፋፋ የመጣውን የሽብርተኝነት፣ የሰዎች ዝውውርና የተደራጁ ወንጀሎች በሀገራትና ህዝቦች ላይ የሚያስከትለውን ስጋትና አደጋ ለመከላከል ሀገራት የተቀናጁ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችላቸውን የትብብር ስምምነት እያደረጉ ይገኛሉ።

 

ኢትዮጵያና ኬንያም በምስራቅ አፍሪካ እያደገ የመጣውን ሽብርተኝነት፣ ህገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች፣ ህገ ወጥ የገንዘብ፣ የሰዎች ዝውውርና የተደራጁ ወንጀሎች በዋነኝነት ለመከላከል በዛሬው ዕለት የመግባቢያ ስምምነት ፈርመዋል።

 

የመግባቢያ ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ በኬንያ በኩል የኬንያ ብሄራዊ መረጃ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ፍሊፕ ካሙሩ ፈርመውታል።

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ በፊርማ ስነ ሥርዓቱ ወቅት እንደገለጹት ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትና ተያያዥ የፀጥታና ደህንነት ችግሮች በተቀናጀ ሁኔታ ለመከላከል ከአብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት ጋር የትብብር ስምምነት መፈጸሟን ጠቁመው እነዚህን የሀገራት ትብብሮች በማጠናከር በክፍለ አህጉሩ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ተናግረዋል።

 

በኬንያ ብሄራዊ መረጃ አገልግሎት የልዑካን ቡድን መሪ / ሰይፍ ሳሌም ሱሌማን በበኩላቸው ሽብርተኝነት፣ ህገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች፣ የገንዘብና የሰዎች ዝውውር እንዲሁም የተደራጁ ወንጀሎች ለምስራቅ አፍሪካ ስጋት በመሆናቸው እነዚህን የቀጠናው ችግሮች ተባብሮና ተቀናጅቶ ለመመከት ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ መሥራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትም ከኬንያ ብሄራዊ መረጃ አገልግሎት ጋር በመሆን አካባቢያዊ ስጋት የሆኑትን ሽብርተኝነት፣ ህገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች ዝውውርን፣ ህገ ወጥ የፋይናንስ ዝውውርን፣ ህገ ወጥ ታጣቂዎችን፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ድንበር ዘለል የተደራጁ ወንጀሎችና ስጋቶችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል የትብብር ስምምነት ሰነድ ውስጥ የተካተቱ ነጥቦች ናቸው።

 

በሰይፍ ሳሊም ሱሌይማን የተመራው የኬንያ ብሄራዊ መረጃ አገልግሎት የልዑካን ቡድን ከትናንት ጀምሮ በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትና ሳይንስ ሙዚየምንና የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ተቋማትን በዛሬው ዕለት ጉብኝቷል።

 

ኢትዮጵያና ኬንያ ወዳጅነት ያላቸው የጎረቤት ሀገራት ሲሆኑ ለረጅም ጊዜ በፖለቲካው፣ ኢኮኖሚውና ማህበራዊ ዘርፎች መልካም የሚባል ግንኙነት አላቸው።

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች