የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የሱዳን ጠቅላላ የደህንነት አገልግሎት በጋራ ለመስራት የሚስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የሱዳን ጠቅላላ የደህንነት አገልግሎት በጋራ ለመስራት የሚስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።    

 

በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ከሱዳን ጠቅላላ የደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አህመድ ኢብራሂም አሊ ሙፍዲል እና ሌሎች ከፍተኛ የተቋሙ አመራሮች ጋር በመረጃና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ በካርቱም መክረዋል።      

ሁለቱ የመረጃና ደህንነት ተቋማት ግንኙነታቸውን አጠናክረው በጋራ መስራት ለሁለቱ ጎረቤት ሀገራት እና ህዝቦች ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ስለሚኖረው ጉልህ አስተዋጽኦ በጥልቀት መክረዋል።

 

ከውይይቱ በኋላም ሁለቱ ተቋማት የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መረጃ ለመለዋወጥ እና በጋራ ለመስራት የሚስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። 

 

የስምምነቱ ትኩረትም ተቋማቱ በጋራ በሆኑ ጉዳዬች ላይ የተሞክሮ እና መረጃ ለመለዋወጥ፣ የቀጠናው የጋራ ስጋት የሆነውን ሽብርተኝነት በጋራ መዋጋት፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ መከላከል፣ የሁለቱ ሀገራት ዜጎች በሰላም የመኖርና የመንቀሳቀስ ደህንነትን ማረጋገጥ እና የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ሰላም የሚጎዱ አካላትን በጋራ መከላከል ላይ በትብብር ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል።   

 

በአቶ ተመስገን ጥሩነህ የሚመራው የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት አገልግሎት የልዑካን ቡድን በካርቱም ለሁለት ቀናት በነበረው ይፋዊ የስራ ጉብኝት ከሱዳን ልአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱል ፈታ አልቡራህምንና ከልአላዊ ምክር ቤቱ ምክትል ሊቀመንበር ሞሐመድ አምዳን ዳጋሎ ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት ሰላምና ደኀንነት ዙሪያ መወያዩቱን አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ አመልክቷል።

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች