በደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማርዲያት የብሄራዊ ደኅንነት ልዩ አማካሪ የሚመራ የደቡብ ሱዳን ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማርዲያት የብሄራዊ ደኅንነት ልዩ አማካሪ በሆኑት ኮንግ ቲፕቲፕ ጋትሉዋክ የሚመራው የደቡብ ሱዳን ልዑካን ቡድን ትናንት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብቷል።

 

የደቡብ ሱዳን ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ሲገባ የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር አቀባበል አድርገውለታል

 

የልዑካን ቡድኑ በዛሬው ዕለት የታላቁ ህዳሴ ግድብን የጎበኘ ሲሆን በብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሥር በሚገኘው የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ በማከናወን በኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሸራ መርሃ ግብር ላይ ተሳትፈዋል።

 

በተጨማሪም የደቡብ ሱዳን ልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሪፎርም ሥራዎች ውጤቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል ነገና ከነገ ወዲያ በሚኖራቸው መርሃ ግብርም የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን ጨምሮ የሌሎች የፀጥታና ደኅንነት ተቋማትን እንደሚጎበኙ ተገልጿል

 

ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ሀገራት የህዝብ ለህዝብና የመንግሥታት ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ በመምጣታቸው በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ፀጥታን በማረጋገጥ እንዲሁም ሽብርተኝነትን በመከላከል ረገድ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ ስምምነቶች ይፈጽማሉ ተብሎም ከወዲሁ ይጠበቃል

 

የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የልዑካን ቡድኑ በደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት የብሄራዊ ደኅንነት ጉዳዮች ልዩ አማካሪ በሆኑት ኮንግ ቲፕቲፕ ጋትሉዋክ የተመራ ሲሆን የደቡብ ሱዳን ናሽናል ሴኩሪቲ ሰርቪስ ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑትን ጀነራል አኮል ኮር ኩክን የደቡብ ሱዳን ጀነራል ኢንተለጀንስ ቢሮ ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑትን ጀነራል ሲሞን የን፣ የደቡብ ሱዳን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ሞሃመድ ሰሎሞን አጎክን እንዲሁም የደቡብ ሱዳን የኢሚግሬሽን ኃላፊን በልዑካን ቡድኑ ማካተቱን የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ አስታውቋል

 

 

 

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች