የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ውጤታማ የመረጃ ስምሪት ማድረጉን ገለጸ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ባለፉት 6 ወራት ስትራቴጂክ እይታውን ካጋጠመው ሀገራዊ የደኅንነት ስጋት አንፃር በመቃኘት ውጤታማ የመረጃ ስምሪት ማድረጉን ገልጿል።

 

መሥሪያ ቤቱ 2014 የሥራ ዘመን የግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ግምገማ በማድረግ በቀጣይ ተግባራት ላይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

 

ባለፉት 6 ወራት በህወሓት የተሰነዘረው ጥቃት ከፍተኛ ሀገራዊ የደኅንነት ስጋት የደቀነባቸው አጋጣሚዎች ተፈጥረው እንደነበር እና ከውጭ ኃይሎች በተከፈተ የተቀናጀ ጫና እና ጣልቃ ገብነትም የኃይል ሚዛንን ለማሳጣት ሙከራ መደረጉን አገልግሎቱ ገልጿል።

 

ተግዳሮቶቹ አጠቃላይ ፖለቲካዊ ውጥረት እና የፀጥታ ችግር ቢደቅኑም የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት አውዳዊ ሁኔታዎችን በመገምገም ስትራቴጂክ እይታውን ካጋጠመው ሀገራዊ የደኅንነት ስጋት አንፃር በመቃኘት ውጤታማ የመረጃ ስምሪት ማድረጉን ገልጿል። በዚህም የሀገርን ኅልውና እና ሉዓላዊነትን ያስጠበቅ ድል መመዝገቡን አብራርቷል።

 

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ በውስጥ እና በውጭ ሃይሎች በተቀናጀ መንገድ የተከፈተውን ጥቃት በመመከት ረገድ ለፌዴራል እና ለክልል የፀጥታ ተቋማት የመረጃ ማዕከል በመሆን የማስተባበር ሚናውን መወጣቱንም ገልጿል። እንደ ሀገር ተደቅኖ የነበረውን የኅልውና ስጋት መቀልበስ ያስቻለ ውጤታማ የመረጃ ስምሪት መከናወኑንም አመልክቷል።

 

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ከወራሪው የህወሓት ኃይል ጋር የተያያዙ የተለያዩ ወታደራዊ ምሥጢሮችን፣ ድብቅ ሴራዎችን እና የሽብር ዕቅዶችን የሚያጋልጡ መረጃዎችን እና ሰነዶችን በመሰብሰብ፣ በማደራጀት እና ተንትኖ ለሚመለከታቸው አካላት በማቅረብ እንደ ሀገር ተደቅኖ የነበረው አደጋ እንዲቀለበስ ተቋማዊ ተልዕኮውን መወጣቱን ነው ያስታወቀው።

 

ለሽብር ቡድኑ መረጃ ሲያቀብሉ የነበሩ በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉም መደረጉንም ጠቁሟል።

 

የሸኔን እና የሌሎችንም ታጣቂዎች እንቅስቃሴዎች ለመግታትም ተቋሙ የመረጃ ስምሪት በመስጠት ሊደርሱ የሚችሉትን ከፍተኛ አደጋዎች ማስቀረቱን ጠቁሟል።

 

ከውጭ የሚቃጣ የሽብርተኝነት አደጋን በመከላከል ረገድ አልሸባብ እና አይኤስ የሚያደርጉትን ምልመላ፣ ስርገት፣ ሥልጠና እና እንቅስቃሴ በተመለከተ መረጃዎችን በመሰብሰብ እርምጃዎች መወሰዳቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመልክቷል።

 

ህገወጥ የጦር መሣሪያዎችን እና የገንዘብ ዝውውርን ጨምሮ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ አሻጥሮችን በመከላከል ረገድም ውጤታማ ኦፕሬሽኖች መካሄዳቸውን አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

 

በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት በአንድ በኩል ፕሮፌሽናል፣ ትውልድ ተሻጋሪ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታጠቀ፣ ብቁ የሰው ኃይል ያለው ተቋም ከማደራጀት ባሻገር ተልዕኮን የሚደግፉ ቁልፍ መሠረተ ልማቶች መገንባታቸውን ያመለከተው መግለጫው፤ በቀጣይም የማስፈጸም አቅምን የሚያዳብሩ ስትራቴጂክ ጉዳዮችን በመለየት አገልግሎት መሥሪያ ቤቱን የማጠናከር ስራ እንደሚሰራ ጠቁሟል።

 

የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት በቀጣዮቹ ጊዜያት ተለዋዋጭ እና ውስብስብ ከሆነው ሀገራዊ የደኅንነት ስጋት አንጻር አደጋን አስቀድሞ በማወቅ ማስቀረት የሚችል ሁለንተናዊ ብቃት መገንባቱን እንደሚቀጥል አመልክቷል።

 

በተለይ ኢኮኖሚያዊ አሻጥር በመሥራት መሠረታዊ ፍጆታዎችን ባልተገባ ዋጋ ለመሸጥ ከሚሞክሩ አካላት ጋር በተያያዘ የችግሮቹን ምንጮች በመለየት የሕግ ተጠያቂነት ማስፈን፤ ፖለቲካዊ ችግሮች ወደ ሀገራዊ የደኅንነት ስጋት እንዳይሸጋገሩ በመረጃ ስምሪት ማገዝ፤ ከውጭ ሊቃጡ የሚችሉ የብሔራዊ ደኅንነት ስጋቶችን በመለየት አስቀድሞ ማክሸፍ የሚያስችል የውጭ መረጃ ስምሪትን ማጠናከር እና ወቅታዊ የደኅንነት ስጋት እየሆነ የመጣውን የመረጃ ጦርነት የሚመክት አቅም መፍጠር ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚሆኑ አስታውቋል።

 

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች