የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ያካሄደው ሥልጠናዊ ግምገማ ተለዋዋጭ የደኅንነት ስጋት በተደቀነበት የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የኢትዮጵያን ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችል ግብዓት እንደተገኘበት አስታወቀ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለአራት ቀናት ያካሄደውን ሥልጠናዊ  ግምገማ አጠናቋል፡፡ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መድረኩን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የተቋሙ መካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች ከተሳተፉበት አመታዊ የአፈጻጸም ግምገማ ጎን ለጎን  በተለያዩ ዓለም አቀፋዊ፣ ቀጣናዊ፣ ሀገራዊና ተቋማዊ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ 

 

በሥነ ልቦና ጦርነት ንድፈ ሐሳብና ተሞክሮዎች፤ በተሻሻለው ዐዋጅ አተገባበር፤ በዓለም አቀፋዊ፣ ቀጣናዊና ሀገራዊ የደኅንነት ስጋቶችና መልካም አጋጣሚዎች፤ በላቀ ተቋማዊና የሰው ኃይል አቅም ግንባታ ዙሪያ   እንዲሁም በሌሎችም ወቅታዊ የመረጃና ደኅንነታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገው ሥልጠና ተለዋዋጭ የደኅንነት ስጋት በተደቀነበት የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የኢትዮጵያን ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ግብዓቶች እንደተገኘበት መግለጫው ጠቁሟል፡፡ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ በተያዘው በጀት ዓመት ያቀዳቸውን የመረጃና የደኅንነት ተልዕኮዎች በላቀ ደረጃ ለመፈጸም  እገዛ እንደሚያደርግም አመልክቷል፡፡

 

መድረኩ የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞችና አመራሮች ተቋማዊ እሴቶችን በመላበስ እንዲሁም በአገልጋይነት መንፈስ ተልዕኮን በመወጣት የኢትዮጵያን ህልውና ለማረጋገጥ አስተዋጽዖ ያበረከቱበት የአፈጻጸም ብቃት በጠንካራ መሰረት ላይ እንዲቆም አቅም እንደሚሆን ያመለከተው መግለጫው፤ በቀጣይም በጥብቅ የሥነ ምግባር መርሕ በመመራት ሀገራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት  የጸና አቋም የተያዘበት እንደነበር አስታውቋል፡፡

 

 በፍጥነት  ተለዋዋጭ የሆነውን  ዓለም  አቀፋዊ ፣አካባቢያዊና ሀገራዊ  ሁኔታዎች በተመለከተ  መረጃዎችን በመሰብሰብ ፣ በመተንተንና ለአስፈጻሚ አካላት በማቅረብ  እንዲሁም ቴክኖሎጂዎችን ለተለያዩ ስምሪቶች በማዋል የደኅንነት  ስጋቶችን በከፍተኛ ደረጃ ለማስቀረትም ዝግጅት መደረጉ የተረጋገጠበትና ቀጣይ አቅጣጫ የተቀመጠበት ሥልጠናዊ ግምገማ እንደነበርም የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መግለጫ አብራርቷል፡፡

 

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ተልዕኮውን  ከወቅታዊ ሀገራዊ የደኅንነት ስጋት አንጻር  በመቃኘት እንዲወጣ ሥልጣንና ኃላፊነት የሚሰጠው የማሻሻያ ዐዋጅ ባለፈው የበጀት ዓመት መጽደቁ ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥር በሥልጠናዊ የግምገማ መድረኩ ተብራርቷል፡፡

 

በዐዋጁ እንደ አዲስ የተሠጠውን የሥነ ልቦና ጦርነትን በተደራጀ መንገድ የመምራት ሥልጣንን ጨምሮ ሌሎችም ተልዕኮዎችን በብቃት ለመፈጸም የሚያግዙ አሠራሮች መዘርጋታቸው፤ አደረጃጀቶች፣ መዋቅሮችና ደንቦችን የማዘጋጀት ተግባራት መጀመራቸው፤  ለሰው ኃይል  አቅም ግንባታ እንዲሁም ስምሪትን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የተከናወኑ ሥራዎች   በሀገር  ውስጥና በአፍሪካ  ቀንድ  አካባቢ ተለዋዋጭና  ውስብስብ  የብሔራዊ ደኅንነት  ስጋቶችን  ለመከላከል  የሚያስችሉ ተጨባጭ አቅሞች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

 

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለአራት ቀናት ያካሄደው ሥልጠናዊ  የግምገማ መድረክ ሲጠናቀቅ በብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ችግኞች በመትከል አረንጓዴ አሻራ የማኖር  መርሐ ግብር የተካሄደ ሲሆን፤ አገልግሎት  መሥሪያ ቤቴ  ምቹ የሥራ  ከባቢ  በመፍጠር  ረገድ  በ2014 የበጀት ዓመት ያከናወናቸው ልዩ ልዩ ተግባራት እና የተቋሙ ዲጂታል ኤግዚብሽን ጎብኝተዋል፡፡

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች