እሴቶችና ግቦች

ተቋማዊ እሴቶቻችን

 

 

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞችን ተቋማዊ ባህል የተመሰረተባቸው መርሆዎች፣ መሰረታዊ እሴቶችና ሙያዊ ፍልስፍናዎች የሚከተሉት ናቸው

 

 

ሀቀኝነት

የላቀ የሞራል ልእልና ባለቤት፣ ቅን፣ ቀጥተኛና ሃቀኛ፣ ቃላችንን የምናከብርና በስራችን እምነት የሚጣልብን እንዲሁም ለተበላሸ ስነምግባር ከሚያጋልጡ አመለካከቶች፣ ተግባሮች፣ ተፅእኖዎችና አዝማሚያዎች ነፃ በመሆን ተልእኮአችንን እንፈፅማለን፣

 

ዝግጁነት

ሙሉ ጊዜያችንና አቅማችንን በመጠቀም ተልእኮኣችንን ለማሳካት እንተጋለን፣ ለሁኔታዎች፣ ክስተቶች፣ ሃሳቦችና የተለያዩ አዝማሚያዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የአካልና የመንፈስ ጥምረት በመፍጠር በፍፁም ተነሳሽነት እንሰራለን፣

ልህቀት

በተሟላ የሙያና እውቀት ልህቀት ላይ በመገኘት ተልእኮአችንን በብቃትና ቅልጥፍና ለመፈፀም እንተጋለን፣ የሰራ አፈፃፀማችንንም በመገምገም ለመማር፣ ልምድ ለመቅሰምና ራሳችንን በማሻሻል ለላቀ ውጤት እንዘጋጃለን፣

 

ምስጢራዊነት

መረጃ የማግኘት አቅማችንን በቀጣይነት ለማሳደግ የኢንፎርሜሽን ምንጮቻችን፣ የድርጊያ ዘዴዎችና አሰራሮቻችንን ምስጢራዊነት እንጠብቃለን፣

መደጋገፍ

ስራችንን በመደጋገፍና በመተባበር እንሰራለን፣ በጋራ ውጤት እናምናለን፣ ብዝሃነትንና አካታችነትን ዋነኛ የተልእኮ አፈፃፀም መሳርያዎቻችን አድርገን እንጠቀማለን፣