የወጣቶች ዞን (Youth Zone)

የወጣቶች ዞን

ተቋሙ በአገሪቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና መሰል ሙያዎች ልዩ ክህሎትና አቅም ያላቸውን ወጣቶች መልምሎ ለማስገባት እንዲያስችለው የበጎ ገጽታ ግንባታ የሚያከናወንበት ነው፡፡ ወጣቶች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የበለጸጉ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለማቅረብ እንዲችሉ

 

   ወጣቶች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የበለጸጉ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለማቅረብ እንዲችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የኢንዶክትሪኔሽን ሥራ ለመሥራት ያግዛል ።

   የመረጃና ደህንነት ዘረፍን ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጋር በማጣመር ለወጣቶች የውድድር መድረክ በመፍጠር በላቀ ሙያና ክህሎታቸው ተመርጠው ወደ ተቋሙ እንዲገቡ ማስቻል ነው ።

   አዲሱ ትውልድ በተቋሙ ላይ የእኔነት ስሜት እንዲያሳድር የሚያስችሉ የጉብኝት መርሃ ግብሮችን ለማካሄድ የሚደረግውን ጥረትን ለማስተዋወቅ ይረዳል ።

 

   በተቋሙ ውስጥ የረጅም ጊዜ አገልግሎት የሠጡ በሥራቸውን ምስጉን የሆኑ አንጋፋ የደህንነትና መረጃ ባለሙያዎች ካሉ በተቋሙ ውስጥ ለሚገኙ ወጣት ሠራተኞች ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉ በማድረግ የአገር ደህንነት፣ ፀጥታንና ህልውናን ለመጠበቅ ምን ያህል ዋጋ እንደሚከፈል ለማሳየት ዕድል ይፈጥራል ።

   በአጠቃላይ አቅም ያላቸው የአገሪቱ አዲስ ትውልድ አባላት በመረጃና ደህንነት ሙያ እንዲያገለግሉ ከፍተኛ ፍላጎት እንዲያድርባቸው የሚያስችል ሚና ይጫወታል ።

   ይህ ሞጁል የወጣቶች የፈጠራ ሥራ ፣ የወጣቶች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክህሎት ውድድር ፣ ጉብኝትና ተሞክሮ የተባሉ አራት ክፍሎች ይኖረዋል ።