Asset Publisher

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከጀርመን የመረጃና ደኀንነት ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት ስምምነት አደረገ
“ወዳጅ እንዲኮራ፣ ጠላት እንዲፈራ መስራት ብቻ ሳይሆን የሰራነውን ማሳየት አለብን‘ አቶ ተመስገን ጥሩነህ
ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

ስለ እኛ

ስለ እኛ

 

ተቋማዊ ራዕይ

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነትና ጥቅሞችን ለመከላከል፣ ለመጠበቅና ለማሳደግ ዓለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የመረጃና ደኅንነት ተቋም መሆን ነው

 

ተቋማዊ ተልእኮ

  ኢትዮጵያን ብሔራዊ ደኅንነትና ጥቅሞች ከማንኛውም ስጋት ለመከላከል፣ ለመጠበቅና    ለማሳካት የሚያስችሉ፡-

  • መረጃዎች መሰብሰብ፣መተንተንና ለሚመለከታቸው የመንግስት አመራሮችና ተቋማት ማቅረብ፤
  • የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ የውጭ ሀገር መሪዎችና ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ደኅንነት መጠበቅና ማስጠበቅ፤
  • በሀገራችንና ህዝቦቿ ጥቅምና ክብር ላይ የሚቃጣ የስነልቦና ጦርነት መከላከልና መቀልበስየሚያስችሉ ስራዎችን መስራት ነው
 

ተቋማዊ እሴቶቻችን

 

  •  
  • ሀቀኝነት
  • ዝግጁነት
  • ልህቀት
  • ምስጢራዊነት
  • መደጋገፍ
  •  

 

Asset Publisher

የወጣቶች ዞን (Youth Zone)

የወጣቶች ዞን

ተቋሙ በአገሪቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና መሰል ሙያዎች ልዩ ክህሎትና አቅም ያላቸውን ወጣቶች መልምሎ ለማስገባት እንዲያስችለው የበጎ ገጽታ ግንባታ የሚያከናወንበት ነው፡፡ ወጣቶች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የበለጸጉ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለማቅረብ እንዲችሉ

 

   ወጣቶች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የበለጸጉ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለማቅረብ እንዲችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የኢንዶክትሪኔሽን ሥራ ለመሥራት ያግዛል ።

   የመረጃና ደህንነት ዘረፍን ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጋር በማጣመር ለወጣቶች የውድድር መድረክ በመፍጠር በላቀ ሙያና ክህሎታቸው ተመርጠው ወደ ተቋሙ እንዲገቡ ማስቻል ነው ።

   አዲሱ ትውልድ በተቋሙ ላይ የእኔነት ስሜት እንዲያሳድር የሚያስችሉ የጉብኝት መርሃ ግብሮችን ለማካሄድ የሚደረግውን ጥረትን ለማስተዋወቅ ይረዳል ።

 

   በተቋሙ ውስጥ የረጅም ጊዜ አገልግሎት የሠጡ በሥራቸውን ምስጉን የሆኑ አንጋፋ የደህንነትና መረጃ ባለሙያዎች ካሉ በተቋሙ ውስጥ ለሚገኙ ወጣት ሠራተኞች ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉ በማድረግ የአገር ደህንነት፣ ፀጥታንና ህልውናን ለመጠበቅ ምን ያህል ዋጋ እንደሚከፈል ለማሳየት ዕድል ይፈጥራል ።

   በአጠቃላይ አቅም ያላቸው የአገሪቱ አዲስ ትውልድ አባላት በመረጃና ደህንነት ሙያ እንዲያገለግሉ ከፍተኛ ፍላጎት እንዲያድርባቸው የሚያስችል ሚና ይጫወታል ።

   ይህ ሞጁል የወጣቶች የፈጠራ ሥራ ፣ የወጣቶች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክህሎት ውድድር ፣ ጉብኝትና ተሞክሮ የተባሉ አራት ክፍሎች ይኖረዋል ።

Asset Publisher

ስለተቋሙ የተነገሩት


ዶክተር አቢይ አህመድ: ጠቅላይ ሚንስትር ​

     


ይህን ተቋም ከፓርቲ ወገንተኝነት ለማላቀቅ ባለፉት ወራት ሰፋፊ ሪፎርም  ሲሰራ ቆይቷል፡፡ እናንተ የኢህአዴግ አባል አይደላችሁም፤ እናንተ የኢህአዴግ ልዩ ወዳጅ  አይደላቹም፡፡ እናንተ እውነተኛ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ህዝቦች ወዳጅ እንዲሁም እያንዳንዱን ዜጋ እና ሃገርን የምትታደጉ የሃገር ተቆርቋሪ እና ሃገር ወዳጅ ዜጋ ብቻ ናችሁ፡፡

                                                                                               


አቶ ተስፋዬ ዳባ: ​ በህ/ተ/ም ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

     


በብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረግነው ቆይታ በጣም  ታሪካዊ ነው፡፡ ከስድስት አመት በላይ ይህን ቋሚ  ኮሚቴ መርቻለሁ፡፡ አንድ ቀንም ቢሆን የአገልግሎቱን ዋና ዳይሬክተር በምክር ቤቱ አይቻቸው አላውቅም፡፡ ምክር ቤቱም በአካልም አያውቃቸውም

                                                                                               


ጀነራል አደም መሃመድ የቀድሞ የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጀነራል

     


በአገሪቱ ከመጣው ለውጥ ጋር ተያይዞ ፈታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙም ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ተጠቃሽ የሆኑ ስኬታማ ተግባራትን እንዳከናወነ የስድስት ወር መደበኛ የስራ አፈጻፀሙን በተመለከተ ውይይት በተደረገበት ወቅት ተገልጿል  ፡፡»