Asset Publisher

null የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

በጉብኝቱ ወቅት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያ ታሪክን ለቀጣይ ትውልድ በማሸጋገር ረገድ ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡

የአገልግሎቱ ምክትል ዳይሬክተር ጀኔራል ሲሳይ ቶላ፤ የአድዋ ድልን የሚመጥን መታሰቢያ መገንባቱ የኢትዮጵያውያን የጋራ ዕሴት የሆኑትን ነፃነትን ያለማስደፈር እንዲሁም የአንድነት መንፈስን ለትውልድ በማሸጋገር ረገድ ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለነፃነታችንና ለአንድነታችን የተከፈለውን መስዋዕትነት ከመዘከር ባለፈ የአሁኑ ትውልድ እያከናወናቸው ያሉ ለመጪው ትውልድ የሚሸጋገሩ ስራዎችንም አስተሳስሮ መያዙ ትርጉም ያለው ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀኔራል ርስቱ ይርዳ በበኩላቸው፤ የአድዋን ታሪክ በአንድ ቦታ አሰባስቦ ለማስተማርና ለትውልዱም ለማሸጋገር በሚያመች መንገድ መታሰቢያው መገንባቱ የሚያኮራ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ስንሰባሰብ ታሪክ መስራት እንደምንችል፣ የሚያሰባስቡን ታላላቅ ጉዳዮች እንዳሉንም ምሳሌ እንደሚሆን አንስተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ፕሮጀክቱ በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የታሪክ ቅብብሎሽ እንዲኖር ታልሞ የተተገበረ መሆኑን ገልፀዋል፡፡