ፎቶ ጋለሪ - መግቢያ - ብሔራዊ መረጃ ማዕከል
Asset Publisher
ስለ እኛ
ስለ እኛ
ተቋማዊ ራዕይ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነትና ጥቅሞችን ለመከላከል፣ ለመጠበቅና ለማሳደግ ዓለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የመረጃና ደኅንነት ተቋም መሆን ነው
ተቋማዊ ተልእኮ
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ደኅንነትና ጥቅሞች ከማንኛውም ስጋት ለመከላከል፣ ለመጠበቅና ለማሳካት የሚያስችሉ፡-
- መረጃዎች መሰብሰብ፣መተንተንና ለሚመለከታቸው የመንግስት አመራሮችና ተቋማት ማቅረብ፤
- የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ የውጭ ሀገር መሪዎችና ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ደኅንነት መጠበቅና ማስጠበቅ፤
- በሀገራችንና ህዝቦቿ ጥቅምና ክብር ላይ የሚቃጣ የስነልቦና ጦርነት መከላከልና መቀልበስየሚያስችሉ ስራዎችን መስራት ነው
ተቋማዊ እሴቶቻችን
- ሀቀኝነት
- ዝግጁነት
- ልህቀት
- ምስጢራዊነት
- መደጋገፍ
Asset Publisher
ቪዲዮዎች
የወጣቶች ዞን (Youth Zone)
የወጣቶች ዞን
ተቋሙ በአገሪቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና መሰል ሙያዎች ልዩ ክህሎትና አቅም ያላቸውን ወጣቶች መልምሎ ለማስገባት እንዲያስችለው የበጎ ገጽታ ግንባታ የሚያከናወንበት ነው፡፡ ወጣቶች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የበለጸጉ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለማቅረብ እንዲችሉ
ወጣቶች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የበለጸጉ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለማቅረብ እንዲችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የኢንዶክትሪኔሽን ሥራ ለመሥራት ያግዛል ።
የመረጃና ደህንነት ዘረፍን ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጋር በማጣመር ለወጣቶች የውድድር መድረክ በመፍጠር በላቀ ሙያና ክህሎታቸው ተመርጠው ወደ ተቋሙ እንዲገቡ ማስቻል ነው ።
አዲሱ ትውልድ በተቋሙ ላይ የእኔነት ስሜት እንዲያሳድር የሚያስችሉ የጉብኝት መርሃ ግብሮችን ለማካሄድ የሚደረግውን ጥረትን ለማስተዋወቅ ይረዳል ።
በተቋሙ ውስጥ የረጅም ጊዜ አገልግሎት የሠጡ በሥራቸውን ምስጉን የሆኑ አንጋፋ የደህንነትና መረጃ ባለሙያዎች ካሉ በተቋሙ ውስጥ ለሚገኙ ወጣት ሠራተኞች ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉ በማድረግ የአገር ደህንነት፣ ፀጥታንና ህልውናን ለመጠበቅ ምን ያህል ዋጋ እንደሚከፈል ለማሳየት ዕድል ይፈጥራል ።
በአጠቃላይ አቅም ያላቸው የአገሪቱ አዲስ ትውልድ አባላት በመረጃና ደህንነት ሙያ እንዲያገለግሉ ከፍተኛ ፍላጎት እንዲያድርባቸው የሚያስችል ሚና ይጫወታል ።
ይህ ሞጁል የወጣቶች የፈጠራ ሥራ ፣ የወጣቶች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክህሎት ውድድር ፣ ጉብኝትና ተሞክሮ የተባሉ አራት ክፍሎች ይኖረዋል ።
Asset Publisher
ስለተቋሙ የተነገሩት
እነዚህ ተቋማት ተፈርተው ሳይሆን ተወደው የሚከበሩ ፤በዚህ ደረጃ ለዜጎች ልብ የቀረቡ ሆነዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
አሁን እያጋጠመን ካለው ፈተና አኳያ ብዙ ጊዜ ሰዎች የማይረዱት እነዚህ ተቋማት በግንባታ ሂደት ላይ ሆነውም በርካታ የተቃጡ እና ሊቃጡ የነበሩ ጥቃቶችን ማምከን መቻላቸውን ነው ። የሚቆጠረው ያጋጠመን ችግር ነው እንጂ የከሸፈውና የመከነው አይደለም
በጣም ከፍተኛ ደስታ ሰጥቶኛል ። በጣም የሚያነቃቃ ትልቅ ስንቅ የሚሆን እና ሌሎችም ተቋማት በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ልክ እራሳችሁን አብቁ ብለን ማስተማር በሚያስችል ደረጃ የተገነባ ተቋም ለማየት ችያለሁ፤ እንኳን ደስ ያላችሁ !ߴߴ