የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር መላው ዓለም በአርዓያነት ሊከተለው የሚገባ ተግባር መሆኑን የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ተወካዮች ገለጹ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 "የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል 6 ጊዜ እየተካሄደ የሚገኘውን የዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ዓላማ የደገፉ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ተወካዮች በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ስር በሚገኘው በብሔራዊ ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኝ ተክለዋል። 

 

የኤምባሲዎቹ ተወካዮች፥ ኢትዮጵያ የምታካሂደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ሥነ-ምህዳር በመፍጠርና የካርበን ልቀትን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት በመሆኑ መላው ዓለም በአርዓያነት ሊከተለው የሚገባ ተግባር ነው ብለዋል።  

 

ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እንዲሰፍንና ደኅንነት እንዲረጋገጥ በማድረግ ረገድ ቁልፍ ሚና የምትጫወት ስትራቴጂክ ሀገር መሆኗን የመሰከሩት የኤምባሲዎቹ ተወካዮች፤ በመረጃ ልውውጥና በተለያዩ የአጋርነት መስኮች የሚደረጉ ትብብሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መጠቆማቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት  መለክታል።

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች