አዲስ አበባ የሚኖሩ አንድ ባለሀብትን በማገት 20 ሚሊዮን ብር የተቀበሉ 7 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

አጋቾቹ 20 ሚሊዮን ብር የተቀበሉት 100 ሚሊዮን ብር ካልከፈላችሁ በሚል ከብዙ ድርድር በኋላ እንደነበር አገልግሎት መስሪያ ቤቱ አስታውቋል

 

አቶ እንግዳው ውዱ የተባሉት ግለሰብ ቡና ወደውጭ በመላክ ሥራ ላይ የተሠማሩ ባለሀብት ናቸው። ግለሰቡ ያላቸውን የሀብት ሁኔታ ሲያጠኑ የቆዩት በእገታው የተሳተፉ ግለሰቦች፤ ስለባለሀብቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ለማጥናት አንድ ተሸከርካሪ በቀን እስከ 1300 ብር ተከራይተው በአዲስ አበባ ውስጥ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመልክቷል።

 

አጋቾቹ ሲያደርጉት የነበረውን ጥናት አጠናቀው ባለሀብቱ እንዲታገቱ ውሳኔ ላይ ከደረሱ በኋላ፤ ግለሰቡን በአዲስ አበባ በተለምዶ ቦሌ ቡልቡላ 93 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሲወጡ መንገድ በመዝጋት አግተው ከአዲስ አበባ ወደ አዋሽ መልካሳ በመውሰድም በታጋቹ ስልክ ለቤተሰብ በመደወል 100 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ መደራደራቸውን የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ይጠቁማል።

 

ይህ ጥቆማ የደረሰው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፤ ታጋቹን በሙሉ ጤንነት፣ እንዲከፍል ከተጠየቀው ገንዘብ ጋር ለመመለስ እና አጋቾችን በቁጥጥር ስር በማዋል በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የመረጃ ኦፊሰሮችን ክትትል እንዲያደርጉ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ኦፕሬሽን እንዲያካሂዱ ስምሪት መስጠቱን አመልክቷል። 

 

ይህ በህቡእ ተደራጅቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰባት አባላት ያሉት የአጋቾች ስብስብ፤ የታጋቹን የአቶ እንግዳው ውዱን ቤተሰቡ 100 ሚሊዮን ብር እንደኪፈል በተደጋጋሚ በሞባይል ስልክ በመደወል ሲወተውት መቆየቱንና አንከፍልም ካሉ ግን ግለሰቡን በመግደል ሬሳውን በር ላይ እንደሚጥሉ ማስጠንቀቃቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መረጃ ይጠቁማል።

 

ይሁንና የታጋቹ ቤተሰቦች 100 ሚሊዮን ብር መክፈል እንደማይችሉ፤ የቤተሰቡን አባወራ ሕይወት ለመታደግ ሲሉ 20 ሚሊዮን ብር እንደሚከፍሉ ያሳውቃሉ ይላል መግለጫው፤ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተል የአጋቾችን መውጫ እና መግቢያ እንዲሁም የግንኙነት መረብ በሚስጥር ሂደቱን ይከታተል እንደነበር በማመልከት።

 

ታዲያ በዚህ መሀል አጋቾቹ የገንዘብ ቅብብሉ በዲጂታል አልያም በባንክ ከሆነ እንያዛለን በሚል ታጋቹን ለመልቀቅ የተስማሙበትን 20 ሚሊዮን ብር ለአያያዝ እንዲመች በሚል በወርቅ እና በዶላር ቀይረው እንዲያቀብሏቸውእና ታጋቹን ለመልቀቅ ይስማማሉ። 

 

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አክሎም፤ ይህን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉት የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ኦፊሰሮች አጋቾችና የታጋች ቤተሰብ ገንዘቡን በምሽት ሲቀባበሉ በቅርበት ሆነው ካረጋጋጡና ታጋቹ ከአዋሽ መልካሳ አዳማ ከተማ ድረስ እንዲመጡ ተደርገው መለቀቃቸውን እና ከቤተሰብ ጋር መቀላቀላቸውን ካረጋገጡ በኋላ ከኦሮሚያ እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በዚህ የአጋች ታጋች የወንጀል መረብ ውስጥ ያሉትን በሙሉ በቁጥጥር ስር ውል እንዲውሉ ማድረጉን አስታውቋል። 

 

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር እንዲውሉና በህግ እንዲጠየቁ ያደረጋቸው በአጋችና ታጋች ወንጀል ውስጥ ሲሳተፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ይበልጣል ካኻሊ ግሩም፣ጎሳዬ ወንድሙ አባተ፣ ስንታየሁ ሞገስ ገብረየሰ፣ አብርሃም ታደሰ ማሞ ፣ደነቀው ቢታው ተገኝ፣ ሙሉቀን ከበደ ታዬ እና የሺዋስ ደበበ ደግፈው የተባሉ ግለሰቦች መሆናቸውን መረጃው ጠቁሟል።

 

አጋቾቹ እራሳቸውን ለመደበቅ እና ከሕግ ተጠያቂት ለማምለጥ ከሶስት በላይ ሓሰተኛ ስሞችና መታወቂያዎችን ለመጠቀም ቢሞክሩም፤ ከፀጥታና ደኅንነት አካላታ መሰዋር እንዳላስቻለቸው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመልክቷል።

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች