በአማራና ትግራይ ክልሎች መካከል የወሰን ይገባኛል ጥያቄን እልባት ለመስጠት ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲሠራ ቆይቷል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በአማራና ትግራይ ክልሎች መካከል የሚገኙና የወሰን ይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸውን አካባቢዎች በህገ መንግስቱ እና በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ መሰረት በዘላቂነት እልባት ለመስጠት በብሔራዊ ደረጃ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲሠራ ቆይቷል።

 

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የሁለቱ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተሳታፊዎች በተገኙበት የብሔራዊ ኮሚቴው አፈፃፀሙ ተገምግሟል።

 

የተፈፀሙና ሊፈፀሙ ሲገባቸው የዘገዩ ጉዳዮች ተነስተው ግምገማ ተደርጎባቸዋል። በግምገማው መሰረት በአፈፃፀም ሂደቱ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተለይተዋል። የማንነትና የይገባኛል ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች ፓለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በአፋጣኝና በዘላቂነት ሊፈታ እንደሚገባም ስምምነት ላይ ተደርሷል።

 

ተፈናቃዮችን በአጭር ጊዜ ወደቀያቸው መመለስ ቅድሚያ ተሰጥቶት በሚፈፀምበት አግባብ ላይ መተማመን ላይ መደረሱም ተጠቁሟል።

 

በብሔራዊ ደረጃ ይህን እንዲያስፈፅም የተቋቋመው ኮሚቴ በቋሚ የጊዜ ሰሌዳ እየተገናኘ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለጉዳዩ እልባት እንዲሰጥ በዛሬው ዕለት በተደረገው ስብሰባ መወሰኑንብሔራዊ ኮሚቴው መረጃ ያመለክታል።

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች