በኢትዮጵያ የአቪዬሽን ደኅንነት ዓለም አቀፍ ኦዲት መካሄድ ጀመረ - ብሔራዊ መረጃ ማዕከል
በኢትዮጵያ የአቪዬሽን ደኅንነት ዓለም አቀፍ ኦዲት መካሄድ ጀመረ
የአቪዬሽን ደህንነት ኦዲቱ ከ12 ዓመታት በኋላ እየተደረገ ያለ ሲሆን፤ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያና በሌሎች የሀገር ውስጥ አውሮፕላን ማረፊያዎች የሚከናወን ነው ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ የሲቪል አቪዬሽን ዘርፉን ደህንነት ለመጠበቅ ከ2 ሺህ በላይ የሰለጠነ የሰው ኃይል መሰማራቱም ተገልጿል።
ከዚህ ባለፈ አውሮፕላን ማረፊያዎች የዓለም አቀፉን የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት መስፈርት ያሟላ የደህንነት መሠረተ ልማት እንዲኖራቸው ተደርጎ እየተሰራ ነውም ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የዓለም አቀፉን የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ስምምነት በመፈረም ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ላለፉት 80 ዓመታት አብሮ እየሰራ መሆኑ በመደረኩ ተነስቷል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ሲሳይ ቶላ፤ በአማካኝ በዓመት ከ10 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን እንዲሁም ከ700 ሺህ ቶን በላይ የካርጎ ጭነት የሚያጓጉዘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደኅንነትን ማረጋገጥ የአገልግሎት መስሪያ ቤታችን ቀዳሚ ተግባር ነው ብለዋል።
አክለውም፤ የዓለም አቀፉን የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ኦዲተሮች ለስራቸው አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም ገልፀዋል።
በመድረኩ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ሲሳይ ቶላ፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዴኤታ ዴንጌ ቦሩ፣ የዓለምአቀፉ የአቪዬሽን ድርጅት ኦዲተሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።