"የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ብሔራዊ ደኅንነትንና ጥቅምን በመጠበቅ ኢትዮጵያን የሚያሻግር ተቋም እየገነባ ነው" - የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሀገሪቱ ካለችበት ፈታኝ ሁኔታ አንጻር ብሔራዊ ደኅንነትንና ጥቅምን በመጠበቅ ኢትዮጵያን የሚያሻግር ተቋም እየገነባ ካለው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ተሞክሮ መቅሰማቸውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለፁ።

 

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የተመሩ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ ዲኖች፣ዳይሬክተሮችና ምክትል ዳይሬክተሮች የሉዑካን ቡደን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን የሪፎርምና የተልዕኮ ሥራዎች መጎብኘታቸውን የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መረጃ አመልክቷል፡፡

 

የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ እንዳመለከተው፤ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንትና ከፍተኛ አመራሮች በጉብኝታቸው የተቆሙን ሪፎርምና ተልዕኮ የሚያስቃኛውን ዲጂታል ኤግዚብሽን፣ ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የተከናውኑ ተግባራትን ጨምሮ ዘመን ተሻጋሪ ተቋም ለመገንባት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ 

 

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌና ሉዑካኖቻቸው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባካሄደው ሁሉን አቀፍ ሪፎርም በፈታኝ ሀገራዊ ሁኔታ ውስጥ እያለፈ ቴክኖሎጂ በመጠቀምና በማበልጸግ፤ በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፤ ዘመናዊ የአሠራር ስርዓቶች በመዘርጋት፤ አጋርነትና ትብብርን በማጠናከር እንዲሁም ምቹ የሥራ ሁኔታ በመፍጠር ረገድ በርካታ ተግባራት ማከናወኑን ከጉብኝታቸው እንደተገነዘቡ ገልጸዋል፡፡  

 

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን የጀመረውን መንገድ ለማሳከት የሚያገለግል ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ግብዓት ማግኘታቸውንና ተሞክሮ መቅሰማቸውን አመልክተዋል፡፡

 

ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ በተቋም ግንባታ ረገድ በጋራ ለመሥራት የሚያግዛቸውን መስመር አጠናክረው ለመቀጠል ጉብኝቱ መልካም አጋጣሚ የፈጠረ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌና የልዑካን ቡድኑ አባላት በተለይ በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፤ በምርምርና ጥናት እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ በመሆን ለመደራጀት የሚረዱ ጉዳዮችን በመለየት ትብብራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሳድጉ ጠቁመዋል፡፡ 

 

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ያደረጉት ጉብኝት ሀገራዊ ደኅንነትን በማረጋገጥ ረገድ የድርሻቸውን ለማበርከት በላቀ ደረጃ መነሳሳት ይፈጥራል ብለዋል፡፡

 

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመረጃና ደኅንነትን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት ሊደግፍ የሚችል እምቅ አቅም እንዳለው የገለጹት አቶ ተመስገን፤ በተለይ ውስብስብ የሆነውን ሀገራዊ ደኅንነት የማረጋገጡን ተግባር በምርምር ሥራ፣ በቴክኖሎጂና የሰው ኃይል በማብቃት ማገዝ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡ 

 

በዚህ ረገድ የተቋሙ የጥናትና የምርምር ማዕከል ከሆነው ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ጋር በትብብር የሚሠሩ ተግባራት እንደሚጠናከሩ መግለጻቸውን በላከው መረጃ አመልክቷል፡፡

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች