በደኅንነትና በሀገራዊ ጥቅም ዙሪያ አበክረው የሚሠሩ የዲፕሎማቲክ ሰራተኞችን መፍጠር የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለፀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በደኅንነትና በሀገራዊ ጥቅም ዙሪያ አበክረው የሚሠሩ የዲፕሎማቲክ ሰራተኞች መፍጠር ሀገራዊ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት /ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ሲሳይ ቶላ ገለጹ፡፡

 

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አዲስ ለተሾሙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በዛሬው እለት በሀገራዊ ደኅንነትና ጥቅሞች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

 

ስልጠናውን የወሰዱት አዲስ የተሾሙ አምባሳደሮች የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ተቋምንም ጎብኝተዋል።

 

ስልጠናው በብሔራዊ ጥቅምና ብሔራዊ ደኅንነት፤ በዓለም አቀፍና ቀጣናዊ የደኅንነት አዝማሚያዎችና የኃይል አሰላለፍ፤ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ተቋማትና ኢንተለጀንስ በሚሉና መሰል አጀንዳዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው፡፡

 

ስልጠናውን የሰጡት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት /ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ሲሳይ ቶላ አምባሳደሮቹ በየተሰማሩበት መስክ ተለዋዋጭ የሆነውን የሀገራት ጂዖ-ፖለቲካዊ ፍላጎት መገንዘብና መረዳት ይገባቸዋል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

በደኅንነትና በሀገራዊ ጥቅም ዙሪያ አበክረው የሚሠሩ የዲፕሎማቲክ ሰራተኞች መፍጠር ሀገራዊ ጠቀሜታው የጎላ ነው ያሉት አቶ ሲሳይ ቶላ፤ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ወክለው ተልዕኮ ለሚወስዱ ሰራተኞች የሚያደርገውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

 

ስልጠናውን የተከታተሉና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን የጎበኙት አምባሳደሮቹ የወሰዱት ስልጠናና አገልግሎት መስሪያ ቤቱን መጎብኘታቸው የሀገራቸውን ጥቅም ለማስከበር ለሚያደርጉት ጥረት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

 

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች