የተለየ ክህሎትና ብቃት ያለው ኃይል መገንባቱ ግጭት ጠማቂዎችን ለመቆጣጠር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የተለየ ክህሎት ትጥቅና ብቃት ያለው ኃይል መገንባቱ ግጭት ጠማቂዎችን ለመቆጣጠርና መረጃ ለመሰብሰብ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

 

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ያሰለጠናቸውን የልዩ ኢንተለጀንስ ኦፕሬሽን ዩኒት አባላትን   አስመርቋል።

 

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ እንዲሁም የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ሲሳይ ቶላን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በምርቃቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል። 

 

በመልዕክታቸውም፤ ስልጠናው በሀገራችን ውስጥ አንድ ትልቅ እድገትና እምርታ መሆኑን ገልጸዋል።

 

የተለየ ክህሎት ትጥቅና ብቃት ያለው ኃይል መገንባቱ ግጭት ጠማቂዎችን ለመቆጣጠርና መረጃ ለመሰብሰብ ጥልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ 

 

በቀጣይም መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል፡፡

 

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው ሰልጣኞቹ የተሸከሙት አደራ ምን እንደሆነ መገንዘባቸውን ገልጸዋል።  

 

በተጨማሪም ሰልጣኞች በቀጣይነት ራሳቸውን ማብቃት እንደሚገባቸው መገንዘባቸውንና ሌሎች ሰልጣኞችን ደግሞ በብዛት ማፍራት አንዳለባቸው ገልጸዋል። 

 

ሰልጣኞች በማንኛውም የአየር ሁኔታ ውስጥ ሆነው አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ተቋቁመው የተሰጣቸውን ተልዕኮ መወጣት የሚያስችላቸው ብቃትን የሚያላብስ አቅም ገንብተዋል ያሉት ደግሞ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ሲሳይ ቶላ ናቸው። 

 

ሰልጣኞች ልዩ ልዩ ቴክኖሎጂዎችንና መሳሪያዎችን በመጠቀም ከተልዕኮ አካባቢዎች ጋር በመመሳሰል ጠላትን በማጥቃት መረጃ መንትፎ የማምጣት ብቃት ገንብተዋል ማለታቸውን ዘግቧል።

 

አስፈላጊ ከሆነም የደፈጣ ውጊያ የማድረግና ራሳቸውን የመከላከል ብቃት መገንባታቸውንም ገልጸዋል። 

 

በተጨማሪም የተጠረጠረ ሰው ወይም ተሽከርካሪን በመክበብ በቁጥጥር ስር በማዋልና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን የመውሰድ ስልቶችን በስልጠና ቆይታቸው ማግኘታቸውን ገልጸው፤ በዚህም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት እንደሚወጡ በልበ ሙሉነት መናገር ይቻላል ብለዋል።

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች