የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮርያ የመረጃና ደኅንነት ተቋማት ሽብርተኝነትና  ድንበር ተሻጋሪ   ወንጀሎችን  በጋራ  ለመከላከል  ተስማሙ 

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መረጃ እንዳስታወቀው  የአገልግሎቱ ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በደቡብ ኮርያ የሥራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፤ ከሀገሪቱ  አቻቸው ቴዮንግ ቾ ጋር በደቡብ ኮርያ ሴኦል ከተማ ተገናኝተው በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር  አድርገዋል።

 

የኢትዮጵያና የደቡብ ኮርያ የመረጃና ደኅንነት ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ የስጋት ደረጃው እያደገ  የመጣውን  ሽብርተኝነትን እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነትም መፈራረማቸውን የጠቆመው መረጃው፤ ለተግባራዊነቱ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩም ማረጋገጣቸውን አስታውቋል፡፡

 

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከደቡብ ኮርያ  አቻቸው ቴዮንግ ቾ  በቀጣናዊና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይም  የተወያዩ ሲሆን፤ በሁለቱ ሀገራት የመረጃና ደኅንነት ተቋማት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር በስትራቴጂካዊ አጋርነት  ደረጃ በማጠናከር እና የመረጃ ልውውጥን በማሳደግ የጋራ የሆኑ ስጋቶችን   ለመፍታት እንደሚሠሩም ተመልክቷል፡፡

 

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ እ. አ. አ በ1963 ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ  በሁለቱ ኮርያዎች ጦርነት ወቅት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት  የሰላም አስከባሪ ጦር በመላክ  ባደረገችው  አስተዋጽኦ  በሀገራቱ መካከል ጠንካራ ትስስርና ትብብር መፈጠሩን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙኃን የላከው መረጃ አመልክቷል፡፡ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ ዘማቾች የተገነባውን የመታሰቢያ ሙዚየም መጎብኘታቸውንም  ጠቁሟል፡፡

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች