የብሔራዊ መረጃ ደኅንነት አገልግሎት እንደ ተቋም የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ ስራ አስጀመረ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የብሔራዊ መረጃ ደኅንነት አገልግሎት እንደ ተቋም የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ ስራዎችን በችግኝ ተከላ አስጀምሯል።

 

የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መከላከል እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ አንድ የብሔራዊ ደህንነትን ማስጠበቅ አካል በመሆኑ አገልግሎቱ የአረንጓዴ አሻራ ስራን ከሠራተኞቹ ጋር በመሆን ለተግባራዊነቱ እንደሚተጋ አስታውቋል።

 

ኢትዮጵያ ያሏትን የተፈጥሮ ፀጋዎች መጠበቅ እና ማበልፀግ ደህንነቷን አስተማማኝ ማድረግ በመሆኑ በዚህ ረገድ አገልግሎቱ የበኩሉን እንደሚወጣም ነው የገለፀው።

 

የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል ሲሳይ ቶላ፤ የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ በሚፈጠር የምግብ እጥረት፣ የተፈጥሮ ሀብት መራቆት እና መሠል ችግሮች በሀገራት የደህንነት ቀውስ እየፈጠረ በመሆኑ የአረንጓዴ አሻራ ስራ አንደኛው ዘላቂ የመፍትሄ አማራጭ ነው ብለዋል።

 

በዚህ መነሻነት የተጀመሩ ስራዎችን ለማጠናከር በማለምም አገልግሎቱ የአረንጓዴ አሻራ ስራ ከተጀመረ አንስቶ 500 ሺህ ችግኞች መተከላቸውን አብራርተዋል።

 

የአገልግሎቱ ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል ታዜር ገብረ እግዚአብሔር በበኩላቸው፤ የአረንጓዴ አሻራ ስራ ከተጀመረ ወዲህ ችግኞችን በዘመቻም ከዘመቻ ውጭ ባለ መንገድም መትከል ባህል እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

 

አለም በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ምክንያት እያጋጠማት ያለውን ስጋት በመቅረፍ ሀብት የመፍጠር እና የማብዛት ስራን በማከናወን ኢትዮጵያ አርአያነት ያለዉ ስራን እየሠራች መሆኑን ገልፀዋል።

 

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል ርስቱ ይርዳው፤ በዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ አገልግሎቱ 70 በላይ ችግኞችን ተከላ በማከናወን ላይ መሆኑን ጠቁመው፤ የልማት ጉዳይ ከደህንነት ጉዳይ ተነጥሎ የማይታይ መሆኑን አክለዋል። ( ኢብኮ )

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች