ለ37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ደኅንነቱ የተረጋገጠ መስተንግዶ ለማድረግ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

በቅርቡ በሚካሄደው 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለሚሳተፉ እንግዶች ደኅንነቱ የተረጋገጠ መስተንግዶ ለማድረግ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ላይ ቅንጅታዊ አመራር ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን የብሔራዊ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኮሚቴ ገለጸ።

 

ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኮሚቴ በይፋ ስራ በመጀመረበት መድረክ ላይ፥ በቅርቡ የሚደረገው 37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ደኅንነቱ በተረጋገጠ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው መስክ ቅንጅት እና ርብርብ በማድረግ ውጤታማ አመራር ለመስጠት አቅጣጫ ተቀምጧል።

 

የአቪዬሽን ዘርፍ የሴኪዩሪቲ ሥራና ዝግጁነት ሁሌም በንቃት የሚተገበር ቢሆንም፤ 12 ዓመት በኋላ በሰኔ ወር ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ለሚደረገው ሀገራዊ ኦዲት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ተመልክቷል።

 

የዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ለሚያደርገው ኦዲት ሁሉም የኮሚቴው አባል ተቋማት አስፈላጊውን ድጋፍ እና ትብብር ለማድረግ የድርሻ ተግባራትን በመውሰድ በቼክሊስት ክትትል የሚደረግበት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም ተመልክቷል።

 

የኮሚቴው ሰብሳቢና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ ሲሳይ ቶላ በመክክር መድረኩ ላይ እንደገለጹት፥ ኢትዮጵያ የምትጠቀምባቸው ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ኤርፖርቶች አገልግሎትና የአየር ክልል ቁጥጥርን በሚመለከት በቅርቡ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ካናዳ እና እስራኤልን ጨምሮ 10 ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኦዲቶች ያለ ምንም አሉታዊ ግኝት ማለፍ መቻሉን አመልክተዋል።

 

ቢሆንም በየጊዜው ተለዋዋጭ በሆነው የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ እና በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎት ውስጥ የብሔራዊ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኮሚቴ ሥራውን በይፋ መጀመሩ ኢንዱስትሪውን ለማዘመን እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን እና ውሳኔዎችን ለመስጠት እንዲሁም ቅንጅታዊ አመራር ለመዘርጋት ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ብለዋል።

 

ብሔራዊ ኮሚቴው ከመቋቋሙ አስቀድሞ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መሪነት በአቪዬሽን ዘርፉ ተግባራዊ በተደረጉ የሪፎርም ሥራዎች ስር ነቀል ለውጥ በመከናወኑ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ያመለከቱት አቶ ሲሳይ፤ በእነዚህ የሪፎርም ስራዎችም 2015 . ጀምሮ እስካሁን ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 1230 . የአደንዛዥ ዕፅ፤ በሀገራችን የምንዛሬ ዋጋ ሲተመን 95 ሚሊዮን ብር ገደማ የተለያዩ ሀገራት ሕገ-ወጥ ገንዘብ እንዲሁም 125 ድሮን፣ 428 ባይኖኩላር እና ሌሎችም ለታጣቂዎች የሚውሉ የቴክኖሎጂና የስለላ መሳሪያዎች በቁጥጥር ማዋል መቻሉን ገልጸዋል።

 

የብሔራዊ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኮሚቴ ከአቪዬሽን ደኅንነት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮችን ጨምሮ 10 ተቋማትን በአባልነት ያካተተ ኮሚቴ ነው።

 

ለግማሽ ቀን የተካሄደው የብሔራዊ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኮሚቴ ስብሰባ የኮሚቴውን መተዳደሪያ መመሪያ በማጽደቅና የተለያዩ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መጠናቀቁን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ አመልክቷል።

 

ሀገራችን ኢትዮጵያ .. 1944 የዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅትን (ICAO) በመቀላቀል ከአፍሪካ የመጀመሪያዋ የድርጅቱ ፈራሚ አባል ሀገር መሆኗ ይታወሳል።

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች