ኢትዮጵያና ኬንያ የመረጃ ልውውጥና የጋራ ኦፕሬሽን አጠናክረው ለመቀጠል ተስማሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያና የኬንያ የደኅንነት ተቋማት ቀጣናዊ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን የመረጃ ልውውጥና የጋራ ኦፕሬሽን አጠናክረው ለመቀጠል መስማማታቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት አገልገሎት አስታወቀ፡፡

 

የኬንያ ናሽናል ኢንተለጀንስ ሰርቪስ ዳይሬክተር ጀነራል ኖርዲ ሐጂ ዛሬ ጠዋት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህና ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

 

የኢትዮጵያና የኬንያ የመረጃና የደኅንነት ተቋማት በወቅታዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ምክከር ያደረጉ ሲሆን፤ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያና የኬንያ ወንድማማች ሕዝብ ለዘመናት የዘለቀ የአብሮነት ታሪክ እንዳላቸው አስታውሰዋል፡፡

 

የሁለቱ ሀገራት አቻ ተቋማትም ጠንካራ ትብብር እንዳላቸውና ይህንንም አስጠብቀው መዝለቃቸውን ገልጸዋል፡፡

 

የኢትዮጵያና የኬንያ የመረጃና የደኅንነት ተቋማት በመረጃ ልውውጥና በተለያዩ መስኮች የሚያደርጉትን ትብብርም በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል ቁርጥኝነት መኖሩን ያመለከቱት አቶ ተመስገን፤ በዚህም በቀጣናው የሚገኙ ሀገራትን ጥቅም ያማከሉ የአጋርነት ማዕቀፎች የትኩረት ማዕከል እንደሚሆኑ አስታውቀዋል፡፡

 

የኢትዮጵያና የኬንያ አቻ ተቋማት በድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች፣ በአቅም ግንባታ መስኮች፣ በሕገወጥ የጦር መሣሪያና የሰዎች ዝውውር ዙሪያ መረጃዎችን በመለዋወጥና የጋራ ኦፕሬሽኖችን በማካሄድ ቀጣናዊ ሰላምንና ደኅንነትን ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ በትብብር ለመሥራት መስማማታቸውን አቶ ተመስገን ጠቁመዋል፡፡

 

በተለይ ሽብርተኝነትን በመከላከልና በመመከት ረገድ መረጃዎችን ከመለዋወጥና የጋራ ኦፕሬሽኖችን ከመምራት ባሻገር ወቅታዊ የሥጋት ምንጮችን በመለየት ተሞክሮዎችን ለመጋራትና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት በላቀ ደረጃ እንደሚጠናከሩ አስታውቀዋል፡፡

 

የኬንያ ናሽናል ኢንተለጀንስ ሰርቪስ ዳይሬክተር ጀነራል ኖርዲ ሐጂ በበኩላቸው፤ የሁለቱ ሀገራት የመረጃና የደኅንነት ተቋማት ሽብርተኝነትንና ድንበር ዘለል ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል የተቀናጀ ስምሪት እያካሄዱ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ 

 

በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የሚታዩ የደኅንነት ሥጋቶችን ለመከላከል የሁለቱ ሀገራት ትብብርና ጥምረት ወሳኝ ሚና አለው ያሉት የኬንያ ናሽናል ኢንተለጀንስ ሰርቪስ ዳይሬክተር ጀነራል ኖርዲ ሐጂ፤ በተለይ ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመከላከል ረገድ ያላትን ውጤታማ ተሞክሮ እንደ ግብዓት በመውሰድ የመረጃ ልውውጥና የጋራ ኦፕሬሽኖች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል፡፡

 

በቀጣናው የሚታዩ የደኅንነት ሥጋቶችን አስቀድሞ በማወቅ ለመከላከል የሚከናወኑ ቅንጅታዊ ሥምሪቶች የጋራ ጥቅምን ለማስጠበቅ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ያመለከቱት የኬንያ ናሽናል ኢንተለጀንስ ሰርቪስ ዳይሬክተር ጀነራል ኖርዲ ሐጂ፤ የሁለቱ ሀገራት የመረጃና ደኅንነት ተቋማት የትብብርና የአጋርነት መስኮች ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማስታወቃቸዉን የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት አገልገሎት ለመገናኛ ብዙሃን የላከዉ መረጃ አመልክቷል።  

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች