በአቶ ተመስገን ጥሩነህ አመራር ሰጪነት በተቋሙ የተነገቡ የሪፎርምና የተልዕኮ ስራዎችን አስቀጥላለሁ-አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

በአቶ ተመስገን ጥሩነህ አመራር ሰጪነት በተቋሙ የተጀመሩ የሪፎርምና የተልዕኮ ስራዎችን እንደሚያስቀጥሉ አዲስ የተሾሙት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ። 

 

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የቀድሞ ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ አዲስ ከተሾሙት የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል።

 

በመርሐ ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ስትራቴጂክ አመራሮች ስለ ተቋሙ የስራ ሁኔታ ገለጻ አድርገዋል።

 

በመርሐ ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንደገለጹት፤ ስትራቴጂክ አመራሩ ሀገር በደኅንነት አጣብቂኝ ውስጥ በገባችበት ወቅት ወደ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ቢቀላቀልም ፈተናዎችን አልፎ በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል።

 

በተለይ በተቋሙ የአመራር አንድነትን በመገንባት በትጋት የሚያገለግልና ለሀገር የሚተርፍ ጠንካራ አመራር መፍጠር መቻሉን ጠቅሰዋል። የአገልግሎት መስሪያ ቤቱን የተልዕኮ ውጤታማነት ለማሳደግና ተደራሽነትና ለማስፋት የተቋቋመበትን አዋጅ በመከለስ ተጨማሪ ተልዕኮዎችን በማከል አመርቂ የስምሪት ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

 

ተቋሙን በሰው ኃይል ለማጠናከር በተከናወኑ ተግባራት አዳዲስ ሰራተኞች ተቋሙን እንዲቀላቀሉ ከማድረግ ባለፈ የተማረና የሰለጠነ የሰው ኃይል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

 

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ቀደም ሲል እራሱን ከሕዝብ ዕይታ ሸሽጎ የቆየ ተቋም እንደነበር ያስታወሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፤ ወደ ሕዝብ ለመቅረብ በተከናወኑ ስራዎች በአሁኑ ወቅት ስለ ተቋሙ በጎ አመለካከት መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል። 

 

እንደ ሀገር ለትውልድ የሚሻገር ተቋም ለመገንባት በተያዘው አቅጣጫ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ውስጥ የተገነባ ስርዓት በመኖሩ ይህን የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በሞራል ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

 

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ሲሳይ ቶላ እንደገለጹት፤ ባለፉት ሶስት ዓመታት ከፍተኛ የመፈጸም አቅም መፈጠሩን፤ ተጽዕኖ ማሳደር የቻለ የተልዕኮ ስምሪት መከናወኑንና በሕዝቡ ዘንድ የነበረውን መጥፎ አመለካከት የቀየረ የገጽታ ግንባታ መከናወኑን አብራርተዋል።

 

ለዚህ ተቋማዊ ስኬት አመራሩ አንድነትና ጥንካሬ እንዲኖረው መደረጉ እንዲሁም በተልዕኮ ስራ ላይ የተፈጠረው ግልጽነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።

 

የአገልግሎቱ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ታዜር ገብረእግዚአብሔር በበኩላቸው ተቋሙ ከቀጣናው ተለዋዋጭ ሁኔታ አንጻር የማድረግ አቅሙን ያጎለበት ቴክኖሎጂ እንዲታጠቅ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በሰው ኃይል እና በተልዕኮ ስምሪት ለማጠናከር በተሰሩ ስራዎች በፖሊሲ ደረጃ የሚፈጥረውን ተጽዕኖ ለማሳደግ መቻሉን አብራርተዋል። 

 

አዲሱ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው ቀደም ሲል በነበራቸው የስራ ኃላፊነትም ሆነ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በለውጥ አመራሩ በተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎች ተቋሙን ቀረብ ብለው ለማውቅ መቻላቸውን ገልጸው፤ አሁን ደግሞ በኃላፊነት ወደ ተቋሙ በመምጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።  

 

በተቋሙ የተጀመሩትን ስኬታማ ስራዎች ለማስቀጠል የተፈጠረውን ለሀገር የማገልገል እና በአንድነት ተቋማዊ ተልዕኮን የማስፈፀም ባህልን ለማጠናከር የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

 

ተቋሙ ከተሰጠው ተልዕኮና ከሚሰራቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች በመነሳት ከሕዝብ ጋር ቀርቦ በመስራት አጋዠነቱን ማጠናከርም ይገባል ማለታቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ አመልክቷል ፡፡

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች