የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አከበረ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች 16ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ መርሐ ግብሮች አክብረዋል፡፡

 

አገልግሎቱ ለመገናኛ ብዙሃን የላከው መረጃ እንደሚያመላክተው "የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው" በሚል መሪ ሐሳብ መሆኑን ነው፡፡

 

የአገልግሎቱ አመራሮችና ሠራተኞች በሀገሪቱ ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ በሚደረጉ ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ጉልህ አስተዋጽዖ በማበርከት የሉዓላዊነትና የአንድነት ምልክት የሆነው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ዛሬም መስዋዕትነት እየከፈሉ መሆኑ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

 

የውስጥና የውጭ ጠላቶች ዛሬም እንደትናንቱ የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ፣ ክብሯን ለማዋረድና ሰንደቅ ዓላማዋን ዝቅ ለማድረግ ጥረት ቢያደርጉም የአገልግሎቱ አመራሮችና ሠራተኞች ክብሯ የተጠበቀ፣ ድንበሯ የታፈረና በወጀብ ውስጥ ፀንታ የምትቆም ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ግንባር ቀደም ሆነው ስምሪታቸውን እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል፡፡

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች