የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሠራተኞች ለመቄዶንያ እና ለጌርጌሴኖን ማዕከላት የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሠራተኞች ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እና ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል የገንዘብ እገዛ አደረጉ።

 

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የተቋሙ ሠራተኞች ያደረጉትን 500 ሺህ ብር በላይ እገዛ ያስረከቡት የተቋሙ ተወካይ በተለያየ ምክንያት ችግር ውስጥ የወደቁ ዜጎችን መደገፍ እንደ ተቋምም ሆነ እንደ ተቋም ሠራተኛ ከፍተኛ ልባዊ እርካታ የሚሰጥ ነው ብለዋል።

 

በመሆኑም የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ እንደዚህ ዓይነት ልገሳዎችን በተደራጀ መንገድ ለማከናወን የሚያስችል ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። 

 

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱም ሆነ መላው ሠራተኞች አቅመ ደካሞችን እንዲሁም ረዳትና ጧሪ የሌላቸው አረጋውያንን በማስታወስ ለወገን ደራሽ ወገን በሚል ተነሳሽነት እገዛውን ማድረጋቸውን አመልክተዋል። 

 

የመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እና የጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ለተደረገው እገዛ ምስጋና አቅርበው፤ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሕዝባዊ ተቋምነቱን እያስመሰከረ በመሆኑ እንደ ዜጋ ኩራት እንደሚሰማቸው ተናግረዋል። 

 

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከዚህ ቀደምም ማኅበራዊ ሀላፊነቱን በመወጣት ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጀቶች እገዛ ሲያከናውን መቆየቱን የጠቆመው መረጃው፤ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክቷል። 

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች