በሰላማዊ ሰልፍ ሽፋን አዲስ አበባን የሁከትና የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ የሽብር ተልዕኮ ተቀብለው በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች ሴራ መክሸፉን የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታወቀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ፅንፈኛ ኃይሎችና የሽብር ቡድኖች በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች በትጥቅ የታገዘ ግፍና ግድያ በመፈፀም እንዲሁም የጸጥታ ችግሮችን በመፍጠር የኅብረተሰቡን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እያወኩ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ፅንፈኛ ኃይሎች እና የሽብር ቡድኖች በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በአንዳንድ አካባቢዎች እየፈፀሙት ያለውን ፀረ- ሰላም እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ መዲና እንዲሁም የዓለም-አቀፍ ተቋማት መቀመጫ ወደ ሆነችው አዲስ አበባም በማስፋፋት በሚፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሀገሪቱን የትርምስ ቀጣና እናደርጋለን በማለት የጥፋት ሴራዎችን አቅደው በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ በተደረጉ የመረጃ ስምሪቶች ተረጋግጧል ብሏል መግለጫው፡፡

በዚህ መነሻነትም ወደ ከተማዋ የታጠቁ ኃይሎችንና ቡድኖችን አስርጎ የማስገባት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን፤ ሰልፍ አናካሂዳለን በሚል ሰበብና ሽፋን ሁከትና ግርግር በመፍጠር ንፁሃንን ኢላማ ያደረግ የሽብር ጥቃት የመፈፀም የተጠና ዕቅድ ይዘው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር መታወቁን የጋራ ግብረ -ኃይሉ መግለጫ አመልክቷል፡፡ ይሄንን እኩይ የጥፋት ሴራ ለመፈጸም ተልዕኮ የወሰዱ 97 ተጠርጣሪዎች በተከናወኑ ኦፕሬሽኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስታውቋል፡፡

የጋራ ግብረ- ኃይሉ መግለጫ፤ እነዚህ ፅንፈኛ ኃይሎች እና ቡድኖች ከዚህ የጥፋት መንገዳቸው እንዲመለሱ ችግሮችና አለመግባባቶችም በውይይት እንዲፈቱ በተደጋጋሚ የተሰጣቸውን እድል ከመጠቀም ይልቅ አሁንም በሕገ-ወጥ ተግባራቸው መቀጠላቸውን አመልክቷል፡፡ መንግሥት በሀገሪቱ ብሎም በመዲናይቱ አዲስ አበባ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል የማያዳግም ሕጋዊ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡

መግለጫው አክሎም፤ የአማራ ክልል ጽንፈኛ ኃይሎች እና የሸኔ የሽብር ቡድን ታጣቂዎችን ሴራ ለማክሸፍ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተቀናጀ ፣ጠንካራና ድንገተኛ ፍተሻ መካሄዱንና ከእነዚህ ጸረ-ሰላም ኃይሎች ጋር በትብብር የሚሠሩ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር እንዲውሉ መደረጉን አመልክቷል፡፡

ለጊዜው የተሰወሩ ተጠርጣሪዎችን አድኖ ለመያዝም የተቀናጀ ክትትልና ስምሪት እየተከናወነ መሆኑን ገልጿል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተካሄደ ድንገተኛ ፍተሻም ሰርገው ወደ ከተማዋ ከገቡ ፅንፈኞችና የሸኔ ሽብር ቡድን አባላት በርካታ የጦር መሣሪያዎች፣ ተቀጣጣይ ፈንጂዎች፣ ቦንቦችና የሬዲዮ መገናኛዎችም ጭምር መያዛቸውን አስታውቋል፡፡

አንዳንድ የውጭ ኃይሎች በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በአንዳንድ አካባቢዎች የሕዝቡን ሰላም እያወኩ ያሉ ጽንፈኛ ኃይሎችንና ሽብርተኛውን ሸኔን እየደገፉ ሀገርን ለማፍረስ እያደረጉ ያለውን እኩይ ሴራ ግብረ -ኃይሉ ደርሶበታል ብሏል መግለጫው። ይህንንም ለማክሸፍ ጠንካራ ሕጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛልም ብሏል።

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል በመግለጫው፤ የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል እየተንቀሳቀሱ ያሉ የውስጥና የውጭ ፀረ- ሰላም ኃይሎችና ቡድኖች ባሰቡት ልክ ወደ ተግባር እንዳይገቡና ፍላጎታቸው እንዲገታ እየተደረገ ባለው ስምሪት ተጋላጭነትን ቀድሞ በማወቅ ሊደርሱ የነበሩ ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳቶችን ማስቀረት ተችሏል ብሏል፡፡

 በዚህ ሂደትም የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት የነበራቸው ትብብር እንዲሁም ተቀናጅቶና ተናቦ የመሥራት ባህል የላቀ እንደነበር አመልክቷል። ኦፕሬሽኖች እንዲሳኩ ሰላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሕዝብ ፀጉረ ልውጦችን፣ ሽብርተኞችንና ሕገ-ወጦችን አጋልጦ በመስጠት ያሳያው ተሳትፎ የሚደነቅ በመሆኑ ለዚህም ላቅ ያለ ምስጋናውን የጋራ ግብረ -ኃይሉ ያቀርባል ብሏል፡፡

በቀጣይም የእነዚህን ፅንፈኛ ኃይሎች እና የሽብር ቡድኖችን እኩይ ዓላማ በማክሸፍ በኩል እየተወሰዱ ያሉ ሕግን የማስከበር እርምጃዎችን በመደገፍና ወንጀለኞችን በማጋለጥ ረገድ ኅብረተሰቡ ሲሰጥ የነበረውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል የጸጥታና የደኅንነት የጋራ- ግብረ ኃይል ጥሪ አቅርቧል።

Asset Publisher

የቅርብ ዜናዎች